የመቅደላ መቶ ሀምሳኛ ዓመት በዓል


የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስን  ሙተ ዓመት መታሰቢያ በተመለከተ  ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ (ሚያዚያ 12/8-15/2010 . በቀጣይ  2010 . ሚያዚያ ወር ላይ  150  ዓመት  የአፄ ቴዎድሮስ  ሙተ ዓመት በመቅደላ  በስፋት ይከበራል፡፡ የመቅደላ ታሪካዊ ጦርነትና  የንጉስ ቴዎድሮስ መሞት 19ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያና አፍሪካ አህጉር  የወደፊት እጣፈንታን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ አጋጣሚ ነበር፡፡ በዓሉ በተለያዩ  ስርዓቶች የሚከበር ሲሆን የንጉሱን  አስተዳደግ፣  ራዕይና አሟሟት እንዲሁም ንጉሱ በኢትዮጵያውያንና በዓለማቀፍ ፀሃፍት፣በታሪክ ምሁራንና በሰፊው ማህበረሰብ  እንዴት እንደሚታዩ  የተለያየ የመንግስትና የውጭ ሀገር ተቋሟት በተሳተፉበት የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ዓለም አቀፍ ጉባዔው   የቱሪዝም ዘርፉን ይጠቅማሉ በተባሉት አዲስ መስመር በመቅደላ ፣ደብረታቦር፣  ጋፋት ደረስጌና  ቋራ አካባቢዎችን የመጎብኘት ዋነኛ  አካሉ ያደረገ ሲሆን  ባህላዊና ጥበባዊ ስራዎችም በስፋት የሚቀርቡበት ይሆናል፡፡ 

የመቅደላ 150 ዓመት ክብረ በዓል  ለአራት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን  ከሚያዚያ 12- 15 2010 . ከሌሎች ፕሮግራሞች ጋር ጎን ለጎን  የሚካሄድ ይሆናል፡፡  8- ቀናት የሚቆይ   የጉብኝ መርሀ ግብርም ይኖረዋል፡፡ ጉባኤው በጎንደር, ደብረ ታቦርእና አምባ ማቅደላ  የኒቨርስቲ ባለቤትነት  የሚካሄድ ሲሆን ሌሎች የመንግስትም ሆኑ የግል ተቋማት በአጋርነት ይሳተፋሉ፡፡

ምንም እንኳን የጉባኤው ዓላማ ታሪካዊ ክዋኔዎችን መዘከር ቢሆንም የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች    የማህበራዊ ሳይንስ፣ የባህል ፣የስነ ጽሁፍ፣ ቲያትር ፣ሙዚቃ አርኪኦሎጂ ቱሪዝም፣  ስነልሳን፣ ፖለቲካ ሳይንስና የቅርስ አስተዳደር  ባለሙያዎችን የሚያሳትፍ ሲሆን ሌሎች ቅርበት ያላቸውን  የማህበረሰብ ክፍሎች ይጋብዛል፡፡  የጥናት ወረቀቶች ትኩረት ከአፄ ቴዎድሮስ ጋር  በአንድም  ይሁን በሌላ ግንኙነት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡ በተለይ በእርሳቸው የህይወት ታሪክ ለአትዮጵያ የነበራቸው ራዕይ የለውጥ እንቅስቃሴያቸው (የዕውቀት ሽግግር) ንጉሱ ኢትዮጵያ ባህል ውስጥ የነበራቸው  ቦታ ፣በስነ ፅሁፍ፣ በቲያትር፣ በሙዚቃ፣  እና ሌሎችንም ጉዳዮች  የሚይዝ  ይሆናል፡፡   በአጠቃላይ ተመራማሪዎች  የአፄ ቴዎድሮስን  ዘመን ሲያስቡ የሚከተሉት ጉዳዮችና ሌሎችንም  ሊያስታውሱ የግድ ይላቸዋል፡፡ 
ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ በሀገር ውስጥና በውጭ ምሁራን እይታ ፡፡
የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የተሀድሶ  ጉዞና ውድቀት፡፡
የዳግማዊ አፄቴዎድሮስ አሻራዎች ለአሁኑ ትውልድ ያላቸው ጠቀሜታ ፡፡
ከመቅደላ ጦርነትና ከዳግማዊ አፄቴዎድሮስ ሞት በኋላ  ወደ እንግሊዝ ሀገር የተወሰዱት ብሄራዊ ቅርሶች እጣ ፈንታ በተመለከተ፡፡
ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ሀገራቸውን ለማዘመን የወሰዷቸው እርምጃዎች ( የውስጥና የውጭ ግንኙነት)፡፡
ስለዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ስርነቀል እርምጃዎች፡፡